The Quran in Amharic - Surah Qiyamah translated into Amharic, Surah Al-Qiyamah in Amharic. We provide accurate translation of Surah Qiyamah in Amharic - الأمهرية, Verses 40 - Surah Number 75 - Page 577.

| لَا أُقْسِمُ بِيَوْمِ الْقِيَامَةِ (1) (ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡ |
| وَلَا أُقْسِمُ بِالنَّفْسِ اللَّوَّامَةِ (2) (ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡ |
| أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَلَّن نَّجْمَعَ عِظَامَهُ (3) ሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን |
| بَلَىٰ قَادِرِينَ عَلَىٰ أَن نُّسَوِّيَ بَنَانَهُ (4) አይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን (እንሰበስባቸዋለን)፡፡ |
| بَلْ يُرِيدُ الْإِنسَانُ لِيَفْجُرَ أَمَامَهُ (5) ይልቁንም ሰው በፊቱ ባለው ነገር (በትንሣኤ) ሊያስተባብል ይፈልጋል፡፡ |
| يَسْأَلُ أَيَّانَ يَوْمُ الْقِيَامَةِ (6) «የትንሣኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል፡፡ |
| فَإِذَا بَرِقَ الْبَصَرُ (7) ዓይንም በዋለለ ጊዜ፡፡ |
| وَخَسَفَ الْقَمَرُ (8) ጨረቃም በጨለመ ጊዜ፡፡ |
| وَجُمِعَ الشَّمْسُ وَالْقَمَرُ (9) ፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፡፡ |
| يَقُولُ الْإِنسَانُ يَوْمَئِذٍ أَيْنَ الْمَفَرُّ (10) «ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው?» ይላል፡፡ |
| كَلَّا لَا وَزَرَ (11) ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም፡፡ |
| إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ الْمُسْتَقَرُّ (12) በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ |
| يُنَبَّأُ الْإِنسَانُ يَوْمَئِذٍ بِمَا قَدَّمَ وَأَخَّرَ (13) ሰው በዚያ ቀን ባስቀደመውና ባስቆየው ሁሉ ይነገራል፡፡ |
| بَلِ الْإِنسَانُ عَلَىٰ نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ (14) በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)፡፡ |
| وَلَوْ أَلْقَىٰ مَعَاذِيرَهُ (15) ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣም እንኳ (አይሰማም)፡፡ |
| لَا تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ لِتَعْجَلَ بِهِ (16) በእርሱ (በቁርኣን ንባብ) ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ፡፡ |
| إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ (17) (በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡ |
| فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ (18) ባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል፡፡ |
| ثُمَّ إِنَّ عَلَيْنَا بَيَانَهُ (19) ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው፡፡ |
| كَلَّا بَلْ تُحِبُّونَ الْعَاجِلَةَ (20) (ከመጣደፍ) ተከልከል፡፡ ይልቁንም (ሰዎች) ፈጣኒቱን (ዓለም) ትወዳላችሁ፡፡ |
| وَتَذَرُونَ الْآخِرَةَ (21) መጨረሻይቱንም (ዓለም) ትተዋላችሁ፡፡ (አትዘጋጁላትም)፡፡ |
| وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاضِرَةٌ (22) ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡ |
| إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ (23) ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ |
| وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ بَاسِرَةٌ (24) ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡ |
| تَظُنُّ أَن يُفْعَلَ بِهَا فَاقِرَةٌ (25) በርሳቸውም ዐደጋ እንደሚሠራባቸው ያረጋግጣሉ፡፡ |
| كَلَّا إِذَا بَلَغَتِ التَّرَاقِيَ (26) ንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን በደረሰች ጊዜ፤ |
| وَقِيلَ مَنْ ۜ رَاقٍ (27) «አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፡፡ |
| وَظَنَّ أَنَّهُ الْفِرَاقُ (28) (ሕመምተኛው) እርሱ (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መልለየት መኾኑን ባረጋገጠም ጊዜ፡፡ |
| وَالْتَفَّتِ السَّاقُ بِالسَّاقِ (29) ባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፡፡ |
| إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ الْمَسَاقُ (30) በዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ (ፍርድ) ነው፡፡ |
| فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ (31) አላመነምም አልሰገደምም፡፡ |
| وَلَٰكِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ (32) ግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም፡፡ |
| ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰ أَهْلِهِ يَتَمَطَّىٰ (33) ከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ፡፡ |
| أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ (34) የምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፡፡ ለአንተ ተገቢህም ነው፡፡ |
| ثُمَّ أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ (35) ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ለአንተ የተገባህም ነው፡፡ |
| أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَن يُتْرَكَ سُدًى (36) ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን |
| أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِّن مَّنِيٍّ يُمْنَىٰ (37) የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን |
| ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ (38) ከዚያም የረጋ ደም ኾነ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡ |
| فَجَعَلَ مِنْهُ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ (39) ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ፡፡ |
| أَلَيْسَ ذَٰلِكَ بِقَادِرٍ عَلَىٰ أَن يُحْيِيَ الْمَوْتَىٰ (40) ይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን |