The Quran in Amharic - Surah Qariah translated into Amharic, Surah Al-Qariah in Amharic. We provide accurate translation of Surah Qariah in Amharic - الأمهرية, Verses 11 - Surah Number 101 - Page 600.

| الْقَارِعَةُ (1) ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤ |
| مَا الْقَارِعَةُ (2) ምን አስደናቂ ቆርቋሪ ናት |
| وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْقَارِعَةُ (3) ቆርቋሪይቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ |
| يَوْمَ يَكُونُ النَّاسُ كَالْفَرَاشِ الْمَبْثُوثِ (4) ሰዎች እንደ ተበታተነ ቢራቢሮ (ወይም ኩብኩባ) በሚኾኑበት ቀን፤ |
| وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِ الْمَنفُوشِ (5) ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ በሚኾኑበት (ቀን ልቦችን በድንጋጤ ትቆረቁራለች፡፡) |
| فَأَمَّا مَن ثَقُلَتْ مَوَازِينُهُ (6) ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ፤ |
| فَهُوَ فِي عِيشَةٍ رَّاضِيَةٍ (7) እርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፡፡ |
| وَأَمَّا مَنْ خَفَّتْ مَوَازِينُهُ (8) ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ፤ |
| فَأُمُّهُ هَاوِيَةٌ (9) መኖሪያው ሃዊያህ ናት |
| وَمَا أَدْرَاكَ مَا هِيَهْ (10) እርሷም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ |
| نَارٌ حَامِيَةٌ (11) (እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት፡፡ |