The Quran in Amharic - Surah Takathur translated into Amharic, Surah At-Takathur in Amharic. We provide accurate translation of Surah Takathur in Amharic - الأمهرية, Verses 8 - Surah Number 102 - Page 600.

| أَلْهَاكُمُ التَّكَاثُرُ (1) በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡ |
| حَتَّىٰ زُرْتُمُ الْمَقَابِرَ (2) መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ፡፡ |
| كَلَّا سَوْفَ تَعْلَمُونَ (3) ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፡፡ |
| ثُمَّ كَلَّا سَوْفَ تَعْلَمُونَ (4) ከዚያም ተከልከሉ፤ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡ |
| كَلَّا لَوْ تَعْلَمُونَ عِلْمَ الْيَقِينِ (5) በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) እርግጠኛ ዕውቀትን ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልዘናጋችሁ ነበር)፡፡ |
| لَتَرَوُنَّ الْجَحِيمَ (6) ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ፡፡ |
| ثُمَّ لَتَرَوُنَّهَا عَيْنَ الْيَقِينِ (7) ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፡፡ |
| ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ (8) ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ፡፡ |