The Quran in Amharic - Surah Waqiah translated into Amharic, Surah Al-Waqiah in Amharic. We provide accurate translation of Surah Waqiah in Amharic - الأمهرية, Verses 96 - Surah Number 56 - Page 534.
إِذَا وَقَعَتِ الْوَاقِعَةُ (1) መከራይቱ በወደቀች ጊዜ፡፡ |
لَيْسَ لِوَقْعَتِهَا كَاذِبَةٌ (2) ለመውደቋ አስተባባይ (ነፍስ) የለችም፡፡ |
خَافِضَةٌ رَّافِعَةٌ (3) ዝቅ አድራጊና ከፍ አድራጊ ናት፡፡ |
إِذَا رُجَّتِ الْأَرْضُ رَجًّا (4) ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ፡፡ |
وَبُسَّتِ الْجِبَالُ بَسًّا (5) ተራራዎችም መፍፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ (እንደተፈጨ ዱቄት በኾኑ ጊዜ)፡፡ |
فَكَانَتْ هَبَاءً مُّنبَثًّا (6) የተበተነ ብናኝ በኾኑም ጊዜ |
وَكُنتُمْ أَزْوَاجًا ثَلَاثَةً (7) ሦስት ዓይነቶችም በኾናችሁ ጊዜ (ታዋርዳለች፤ ታነሳለችም)፡፡ |
فَأَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ مَا أَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ (8) የቀኝ ጓዶችም ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡ |
وَأَصْحَابُ الْمَشْأَمَةِ مَا أَصْحَابُ الْمَشْأَمَةِ (9) የግራ ጓዶችም ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው፡፡ |
وَالسَّابِقُونَ السَّابِقُونَ (10) (ለበጎ ሥራ) ቀዳሚዎቹም (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ |
أُولَٰئِكَ الْمُقَرَّبُونَ (11) እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡ |
فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ (12) በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲኾኑ፡፡ |
ثُلَّةٌ مِّنَ الْأَوَّلِينَ (13) ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡ |
وَقَلِيلٌ مِّنَ الْآخِرِينَ (14) ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡ |
عَلَىٰ سُرُرٍ مَّوْضُونَةٍ (15) በተታቱ አልጋዎች ላይ ይኾናሉ፡፡ |
مُّتَّكِئِينَ عَلَيْهَا مُتَقَابِلِينَ (16) በእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲኾኑ፡፡ |
يَطُوفُ عَلَيْهِمْ وِلْدَانٌ مُّخَلَّدُونَ (17) በእነርሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡ |
بِأَكْوَابٍ وَأَبَارِيقَ وَكَأْسٍ مِّن مَّعِينٍ (18) ከጠጅ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ)፡፡ |
لَّا يُصَدَّعُونَ عَنْهَا وَلَا يُنزِفُونَ (19) ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡ |
وَفَاكِهَةٍ مِّمَّا يَتَخَيَّرُونَ (20) ከሚመርጡትም ዓይነት በእሸቶች፡፡ |
وَلَحْمِ طَيْرٍ مِّمَّا يَشْتَهُونَ (21) ከሚሹትም በኾነ የበራሪ ሥጋ (ይዞሩባቸዋል)፡፡ |
وَحُورٌ عِينٌ (22) ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡ |
كَأَمْثَالِ اللُّؤْلُؤِ الْمَكْنُونِ (23) ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡ |
جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ (24) በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡ |
لَا يَسْمَعُونَ فِيهَا لَغْوًا وَلَا تَأْثِيمًا (25) በውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መውወንጀልን አይሰሙም፡፡ |
إِلَّا قِيلًا سَلَامًا سَلَامًا (26) ግን ሰላም መባባልን (ይሰማሉ)፡፡ |
وَأَصْحَابُ الْيَمِينِ مَا أَصْحَابُ الْيَمِينِ (27) የቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች |
فِي سِدْرٍ مَّخْضُودٍ (28) በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው፡፡ |
وَطَلْحٍ مَّنضُودٍ (29) (ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም፡፡ |
وَظِلٍّ مَّمْدُودٍ (30) በተዘረጋ ጥላ ሥርም፡፡ |
وَمَاءٍ مَّسْكُوبٍ (31) በሚንቧቧ ውሃ አጠገብም፡፡ |
وَفَاكِهَةٍ كَثِيرَةٍ (32) ብዙ (ዓይነት) በኾኑ ፍራፍሬዎችም፡፡ |
لَّا مَقْطُوعَةٍ وَلَا مَمْنُوعَةٍ (33) የማትቋረጥም የማትከለከልም የኾነች፡፡ |
وَفُرُشٍ مَّرْفُوعَةٍ (34) ከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም (ሴቶችም መካከል)፡፡ |
إِنَّا أَنشَأْنَاهُنَّ إِنشَاءً (35) እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለእነርሱ) ፈጠርናቸው፡፡ |
فَجَعَلْنَاهُنَّ أَبْكَارًا (36) ደናግሎችም አደረግናቸው፡፡ |
عُرُبًا أَتْرَابًا (37) ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደረግናቸው)፡፡ |
لِّأَصْحَابِ الْيَمِينِ (38) ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)፡፡ |
ثُلَّةٌ مِّنَ الْأَوَّلِينَ (39) ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡ |
وَثُلَّةٌ مِّنَ الْآخِرِينَ (40) ከኋለኞቹም ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡ |
وَأَصْحَابُ الشِّمَالِ مَا أَصْحَابُ الشِّمَالِ (41) የግራ ጓደኞችም ምንኛ (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች! ናቸው፡፡ |
فِي سَمُومٍ وَحَمِيمٍ (42) በመርዛም ነፋስ በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው፡፡ |
وَظِلٍّ مِّن يَحْمُومٍ (43) ከጥቁር ጭስም በኾነ ጥላ ውስጥ፡፡ |
لَّا بَارِدٍ وَلَا كَرِيمٍ (44) ቀዝቃዛም መልካምም ያልኾነ፡፡ |
إِنَّهُمْ كَانُوا قَبْلَ ذَٰلِكَ مُتْرَفِينَ (45) እነርሱ ከዚህ በፊት ቅምጥሎች ነበሩና፡፡ |
وَكَانُوا يُصِرُّونَ عَلَى الْحِنثِ الْعَظِيمِ (46) በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና፡፡ |
وَكَانُوا يَقُولُونَ أَئِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَامًا أَإِنَّا لَمَبْعُوثُونَ (47) ይሉም ነበሩ፡- «በሞትንና ዐፈር፣ ዐጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ በእርግጥ የምንቀሰቀስ ነን |
أَوَآبَاؤُنَا الْأَوَّلُونَ (48) «የፊተኞቹ አባቶቻችንም?» |
قُلْ إِنَّ الْأَوَّلِينَ وَالْآخِرِينَ (49) በላቸው፡- «ፊተኞቹም ኋለኞቹም፡፡ |
لَمَجْمُوعُونَ إِلَىٰ مِيقَاتِ يَوْمٍ مَّعْلُومٍ (50) «በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው፡፡ |
ثُمَّ إِنَّكُمْ أَيُّهَا الضَّالُّونَ الْمُكَذِّبُونَ (51) «ከዚያም እናንተ ጠማሞች አስተባባዮች ሆይ |
لَآكِلُونَ مِن شَجَرٍ مِّن زَقُّومٍ (52) « ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ፡፡ |
فَمَالِئُونَ مِنْهَا الْبُطُونَ (53) «ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ፡፡ |
فَشَارِبُونَ عَلَيْهِ مِنَ الْحَمِيمِ (54) «በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችሁ፡፡ |
فَشَارِبُونَ شُرْبَ الْهِيمِ (55) «የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናችሁ፡፡» |
هَٰذَا نُزُلُهُمْ يَوْمَ الدِّينِ (56) ይህ በፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው፡፡ |
نَحْنُ خَلَقْنَاكُمْ فَلَوْلَا تُصَدِّقُونَ (57) እኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን |
أَفَرَأَيْتُم مَّا تُمْنُونَ (58) (በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁን |
أَأَنتُمْ تَخْلُقُونَهُ أَمْ نَحْنُ الْخَالِقُونَ (59) እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን |
نَحْنُ قَدَّرْنَا بَيْنَكُمُ الْمَوْتَ وَمَا نَحْنُ بِمَسْبُوقِينَ (60) እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡ |
عَلَىٰ أَن نُّبَدِّلَ أَمْثَالَكُمْ وَنُنشِئَكُمْ فِي مَا لَا تَعْلَمُونَ (61) ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም (ቅርጽ) እናንተን በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)፡፡ |
وَلَقَدْ عَلِمْتُمُ النَّشْأَةَ الْأُولَىٰ فَلَوْلَا تَذَكَّرُونَ (62) የፊተኛይቱንም አፈጣጠር በእርግጥ ዐውቃችኋል፡፡ አትገነዘቡምን |
أَفَرَأَيْتُم مَّا تَحْرُثُونَ (63) የምትዘሩትንም አያችሁን |
أَأَنتُمْ تَزْرَعُونَهُ أَمْ نَحْنُ الزَّارِعُونَ (64) እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን |
لَوْ نَشَاءُ لَجَعَلْنَاهُ حُطَامًا فَظَلْتُمْ تَفَكَّهُونَ (65) ብነሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባደረግነውና የምትደነቁም በኾናችሁ ነበር፡፡ |
إِنَّا لَمُغْرَمُونَ (66) «እኛ በዕዳ ተያዦች ነን፡፡ |
بَلْ نَحْنُ مَحْرُومُونَ (67) «በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለከልን ነን» (ትሉ ነበር)፡፡ |
أَفَرَأَيْتُمُ الْمَاءَ الَّذِي تَشْرَبُونَ (68) ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አየችሁን |
أَأَنتُمْ أَنزَلْتُمُوهُ مِنَ الْمُزْنِ أَمْ نَحْنُ الْمُنزِلُونَ (69) እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን |
لَوْ نَشَاءُ جَعَلْنَاهُ أُجَاجًا فَلَوْلَا تَشْكُرُونَ (70) ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር፡፡ አታመሰግኑምን |
أَفَرَأَيْتُمُ النَّارَ الَّتِي تُورُونَ (71) ያቺንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን |
أَأَنتُمْ أَنشَأْتُمْ شَجَرَتَهَا أَمْ نَحْنُ الْمُنشِئُونَ (72) እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎችዋ ነን |
نَحْنُ جَعَلْنَاهَا تَذْكِرَةً وَمَتَاعًا لِّلْمُقْوِينَ (73) እኛ (ለገሀናም) ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት፡፡ |
فَسَبِّحْ بِاسْمِ رَبِّكَ الْعَظِيمِ (74) የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡ |
۞ فَلَا أُقْسِمُ بِمَوَاقِعِ النُّجُومِ (75) በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ፡፡ |
وَإِنَّهُ لَقَسَمٌ لَّوْ تَعْلَمُونَ عَظِيمٌ (76) እርሱም ብታወቁ ታላቅ መሓላ ነው፡፡ |
إِنَّهُ لَقُرْآنٌ كَرِيمٌ (77) እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡ |
فِي كِتَابٍ مَّكْنُونٍ (78) በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡ |
لَّا يَمَسُّهُ إِلَّا الْمُطَهَّرُونَ (79) የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡ |
تَنزِيلٌ مِّن رَّبِّ الْعَالَمِينَ (80) ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ |
أَفَبِهَٰذَا الْحَدِيثِ أَنتُم مُّدْهِنُونَ (81) በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን |
وَتَجْعَلُونَ رِزْقَكُمْ أَنَّكُمْ تُكَذِّبُونَ (82) ሲሳያችሁንም (ዝናምን) እናንተ የምታስተባብሉት ታደርጋላችሁን |
فَلَوْلَا إِذَا بَلَغَتِ الْحُلْقُومَ (83) (ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡ |
وَأَنتُمْ حِينَئِذٍ تَنظُرُونَ (84) እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትኾኑ፡፡ |
وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنكُمْ وَلَٰكِن لَّا تُبْصِرُونَ (85) እኛም ግን አታዩም እንጅ ከእናንተ ይልቅ ወደእርሱ የቀረብን ስንኾን፡፡ |
فَلَوْلَا إِن كُنتُمْ غَيْرَ مَدِينِينَ (86) የማትዳኙም ከኾናችሁ፡፡ |
تَرْجِعُونَهَا إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ (87) እውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም፡፡ |
فَأَمَّا إِن كَانَ مِنَ الْمُقَرَّبِينَ (88) (ሟቹ) ከባለሟሎቹ ቢኾንማ፡፡ |
فَرَوْحٌ وَرَيْحَانٌ وَجَنَّتُ نَعِيمٍ (89) (ለእርሱ) ዕረፍት፣ መልካም ሲሳይም፣ የመጠቀሚያ ገነትም አልለው፡፡ |
وَأَمَّا إِن كَانَ مِنْ أَصْحَابِ الْيَمِينِ (90) ከቀኝ ጓዶችም ቢኾንማ፡፡ |
فَسَلَامٌ لَّكَ مِنْ أَصْحَابِ الْيَمِينِ (91) ከቀኝ ጓዶች ስለ ኾንክ ላንተ ሰላም አልለህ (ይባላል)፡፡ |
وَأَمَّا إِن كَانَ مِنَ الْمُكَذِّبِينَ الضَّالِّينَ (92) ከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢኾንማ፡፡ |
فَنُزُلٌ مِّنْ حَمِيمٍ (93) ከፈላ ውሃ የኾነ መስተንግዶ አልለው፡፡ |
وَتَصْلِيَةُ جَحِيمٍ (94) በገሀነም መቃጠልም (አልለው)፡፡ |
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ حَقُّ الْيَقِينِ (95) ይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው፡፡ |
فَسَبِّحْ بِاسْمِ رَبِّكَ الْعَظِيمِ (96) የታላቁንም ጌታህን ስም አወድስ፡፡ |