The Quran in Amharic - Surah Mursalat translated into Amharic, Surah Al-Mursalat in Amharic. We provide accurate translation of Surah Mursalat in Amharic - الأمهرية, Verses 50 - Surah Number 77 - Page 580.

| وَالْمُرْسَلَاتِ عُرْفًا (1) ተከታታይ ኾነው በተላኩት፣ |
| فَالْعَاصِفَاتِ عَصْفًا (2) በኀይል መንፈስን ነፋሾች በኾኑትም፣ |
| وَالنَّاشِرَاتِ نَشْرًا (3) መበተንን በታኞች በኾኑትም፤ (ነፋሶች)፣ |
| فَالْفَارِقَاتِ فَرْقًا (4) መለየትን ለይዎች በኾኑትም፣ |
| فَالْمُلْقِيَاتِ ذِكْرًا (5) መገሠጫን (ወደ ነቢያት) ጣይዎች በኾኑትም፣ |
| عُذْرًا أَوْ نُذْرًا (6) ምክንያትን ለማስወገድ ወይም ለማስፈራራት (ጣይዎች በኾኑት መላእክት) እምላለሁ፡፡ |
| إِنَّمَا تُوعَدُونَ لَوَاقِعٌ (7) ያ የምትስፈራሩበት (ትንሣኤ) በእርግጥ ኋኝ ነው፡፡ |
| فَإِذَا النُّجُومُ طُمِسَتْ (8) ከዋክብትም (ብርሃንዋ) በታበሰች ጊዜ፡፡ |
| وَإِذَا السَّمَاءُ فُرِجَتْ (9) ሰማይም በተከፈተች ጊዜ፡፡ |
| وَإِذَا الْجِبَالُ نُسِفَتْ (10) ጋራዎችም በተንኮተኮቱ ጊዜ፡፡ |
| وَإِذَا الرُّسُلُ أُقِّتَتْ (11) መልክተኞቹም ወቅት በተደረገላቸው ጊዜ፡፡ |
| لِأَيِّ يَوْمٍ أُجِّلَتْ (12) ለየትኛው ቀን ተቀጠሩ (የሚባል ሲኾን)፤ |
| لِيَوْمِ الْفَصْلِ (13) ለመለያው ቀን (በተባለ ጊዜ፤ በፍጡሮች መካከል ይፈረዳል)፡፡ |
| وَمَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الْفَصْلِ (14) የመለያውም ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ |
| وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ (15) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
| أَلَمْ نُهْلِكِ الْأَوَّلِينَ (16) የፊተኞቹን (ሕዝቦች) አላጠፋንምን |
| ثُمَّ نُتْبِعُهُمُ الْآخِرِينَ (17) ከዚያም የኋለኞቹን እናስከትላቸዋለን፡፡ |
| كَذَٰلِكَ نَفْعَلُ بِالْمُجْرِمِينَ (18) በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡ |
| وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ (19) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
| أَلَمْ نَخْلُقكُّم مِّن مَّاءٍ مَّهِينٍ (20) ከደካማ ውሃ አልፈጠርናችሁምን |
| فَجَعَلْنَاهُ فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ (21) በተጠበቀ መርጊያ ውስጥም (በማሕፀን) አደረግነው፡፡ |
| إِلَىٰ قَدَرٍ مَّعْلُومٍ (22) እስከ ታወቀ ልክ ድረስ፡፡ መጠንነውም፤ ምን ያማርንም |
| فَقَدَرْنَا فَنِعْمَ الْقَادِرُونَ (23) መጣኞች ነን |
| وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ (24) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
| أَلَمْ نَجْعَلِ الْأَرْضَ كِفَاتًا (25) ምድርን ሰብሳቢ አላደረግናትምን |
| أَحْيَاءً وَأَمْوَاتًا (26) ሕያዋን ኾናችሁ ሙታንም ኾናችሁ፡፡ |
| وَجَعَلْنَا فِيهَا رَوَاسِيَ شَامِخَاتٍ وَأَسْقَيْنَاكُم مَّاءً فُرَاتًا (27) በውስጧም ከፍተኛዎችን ተራራዎች አደረግን፡፡ ጣፋጭ ውሃንም አጠጣናችሁ፡፡ |
| وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ (28) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
| انطَلِقُوا إِلَىٰ مَا كُنتُم بِهِ تُكَذِّبُونَ (29) «ወደዚያ በእርሱ ታስተባብሉ ወደ ነበራችሁት (ቅጣት) አዝግሙ፡፡ |
| انطَلِقُوا إِلَىٰ ظِلٍّ ذِي ثَلَاثِ شُعَبٍ (30) «ባለ ሦስት ቅርንጫፎች ወደ ኾነው ጥላ አዝግሙ፤» (ይባላሉ)፡፡ |
| لَّا ظَلِيلٍ وَلَا يُغْنِي مِنَ اللَّهَبِ (31) አጠላይ ያልኾነ ከእሳቱም ላንቃ የማያድን ወደ ኾነው (አዝግሙ)፡፡ |
| إِنَّهَا تَرْمِي بِشَرَرٍ كَالْقَصْرِ (32) እርሷ እንደ ታላላቅ ሕንጻ የኾኑን ቃንቄዎች ትወረውራለች፡፡ |
| كَأَنَّهُ جِمَالَتٌ صُفْرٌ (33) (ቃንቄውም) ልክ ዳለቻዎች ግመሎችን ይመስላል፡፡ |
| وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ (34) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
| هَٰذَا يَوْمُ لَا يَنطِقُونَ (35) ይህ የማይናገሩበት ቀን ነው፡፡ |
| وَلَا يُؤْذَنُ لَهُمْ فَيَعْتَذِرُونَ (36) ይቅርታም ይጠይቁ ዘንድ፤ ለእነርሱ አይፈቀድላቸውም፡፡ |
| وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ (37) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
| هَٰذَا يَوْمُ الْفَصْلِ ۖ جَمَعْنَاكُمْ وَالْأَوَّلِينَ (38) ይህ መለያው ቀን ነው፡፡ እናንተንም የፊተኞቹንም ሰብሰብናችሁ፡፡ |
| فَإِن كَانَ لَكُمْ كَيْدٌ فَكِيدُونِ (39) ለናንተም (ለማምለጥ) ብልሃት እንዳላችሁ ተተናኮሉኝ፡፡ |
| وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ (40) ላስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
| إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي ظِلَالٍ وَعُيُونٍ (41) ጥንቁቆቹ በጥላዎችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ |
| وَفَوَاكِهَ مِمَّا يَشْتَهُونَ (42) ከሚከጅሉትም ሁሉ በፍራፍሬዎች ውስጥ ናቸው፡፡ |
| كُلُوا وَاشْرَبُوا هَنِيئًا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ (43) «ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ኾናችሁ ብሉ፣ ጠጡም፤» (ይባላሉ)፡፡ |
| إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ (44) እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ |
| وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ (45) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
| كُلُوا وَتَمَتَّعُوا قَلِيلًا إِنَّكُم مُّجْرِمُونَ (46) ብሉ፤ ጥቂትንም (ጊዜ) ተጠቀሙ፡፡ እናንተ አመጸኞች ናችሁና፡፡ |
| وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ (47) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
| وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ارْكَعُوا لَا يَرْكَعُونَ (48) «ለእነርሱ ስገዱም» በተባሉ ጊዜ አይሰግዱም፡፡ |
| وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ (49) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
| فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَهُ يُؤْمِنُونَ (50) ከእርሱም ሌላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ |