The Quran in Amharic - Surah An Naba translated into Amharic, Surah An-Naba in Amharic. We provide accurate translation of Surah An Naba in Amharic - الأمهرية, Verses 40 - Surah Number 78 - Page 582.

| عَمَّ يَتَسَاءَلُونَ (1) ከምን ነገር ይጠያየቃሉ |
| عَنِ النَّبَإِ الْعَظِيمِ (2) ከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡ |
| الَّذِي هُمْ فِيهِ مُخْتَلِفُونَ (3) ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡ |
| كَلَّا سَيَعْلَمُونَ (4) ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ |
| ثُمَّ كَلَّا سَيَعْلَمُونَ (5) ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡ |
| أَلَمْ نَجْعَلِ الْأَرْضَ مِهَادًا (6) ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን |
| وَالْجِبَالَ أَوْتَادًا (7) ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን |
| وَخَلَقْنَاكُمْ أَزْوَاجًا (8) ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡ |
| وَجَعَلْنَا نَوْمَكُمْ سُبَاتًا (9) እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡ |
| وَجَعَلْنَا اللَّيْلَ لِبَاسًا (10) ሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡ |
| وَجَعَلْنَا النَّهَارَ مَعَاشًا (11) ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡ |
| وَبَنَيْنَا فَوْقَكُمْ سَبْعًا شِدَادًا (12) ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡ |
| وَجَعَلْنَا سِرَاجًا وَهَّاجًا (13) አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡ |
| وَأَنزَلْنَا مِنَ الْمُعْصِرَاتِ مَاءً ثَجَّاجًا (14) ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡ |
| لِّنُخْرِجَ بِهِ حَبًّا وَنَبَاتًا (15) በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡ |
| وَجَنَّاتٍ أَلْفَافًا (16) የተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡ |
| إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ كَانَ مِيقَاتًا (17) የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡ |
| يَوْمَ يُنفَخُ فِي الصُّورِ فَتَأْتُونَ أَفْوَاجًا (18) በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡ |
| وَفُتِحَتِ السَّمَاءُ فَكَانَتْ أَبْوَابًا (19) ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡ |
| وَسُيِّرَتِ الْجِبَالُ فَكَانَتْ سَرَابًا (20) ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡ |
| إِنَّ جَهَنَّمَ كَانَتْ مِرْصَادًا (21) ገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡ |
| لِّلطَّاغِينَ مَآبًا (22) ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡ |
| لَّابِثِينَ فِيهَا أَحْقَابًا (23) በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤ |
| لَّا يَذُوقُونَ فِيهَا بَرْدًا وَلَا شَرَابًا (24) በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡ |
| إِلَّا حَمِيمًا وَغَسَّاقًا (25) ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡ |
| جَزَاءً وِفَاقًا (26) ተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡ |
| إِنَّهُمْ كَانُوا لَا يَرْجُونَ حِسَابًا (27) እነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡ |
| وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا كِذَّابًا (28) በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡ |
| وَكُلَّ شَيْءٍ أَحْصَيْنَاهُ كِتَابًا (29) ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡ |
| فَذُوقُوا فَلَن نَّزِيدَكُمْ إِلَّا عَذَابًا (30) ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡ |
| إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ مَفَازًا (31) ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡ |
| حَدَائِقَ وَأَعْنَابًا (32) አትክልቶችና ወይኖችም፡፡ |
| وَكَوَاعِبَ أَتْرَابًا (33) እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡ |
| وَكَأْسًا دِهَاقًا (34) የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡ |
| لَّا يَسْمَعُونَ فِيهَا لَغْوًا وَلَا كِذَّابًا (35) በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡ |
| جَزَاءً مِّن رَّبِّكَ عَطَاءً حِسَابًا (36) ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡ |
| رَّبِّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا الرَّحْمَٰنِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِنْهُ خِطَابًا (37) የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡ |
| يَوْمَ يَقُومُ الرُّوحُ وَالْمَلَائِكَةُ صَفًّا ۖ لَّا يَتَكَلَّمُونَ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرَّحْمَٰنُ وَقَالَ صَوَابًا (38) መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡ |
| ذَٰلِكَ الْيَوْمُ الْحَقُّ ۖ فَمَن شَاءَ اتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِ مَآبًا (39) ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡ |
| إِنَّا أَنذَرْنَاكُمْ عَذَابًا قَرِيبًا يَوْمَ يَنظُرُ الْمَرْءُ مَا قَدَّمَتْ يَدَاهُ وَيَقُولُ الْكَافِرُ يَا لَيْتَنِي كُنتُ تُرَابًا (40) እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡ |