The Quran in Amharic - Surah Maun translated into Amharic, Surah Al-Maun in Amharic. We provide accurate translation of Surah Maun in Amharic - الأمهرية, Verses 7 - Surah Number 107 - Page 602.

| أَرَأَيْتَ الَّذِي يُكَذِّبُ بِالدِّينِ (1) ያንን በምርመራው የሚያስተባብለውን አየህን? (ዐወቅከውን) |
| فَذَٰلِكَ الَّذِي يَدُعُّ الْيَتِيمَ (2) ይህም ያ የቲምን በኀይል የሚገፈትረው፤ |
| وَلَا يَحُضُّ عَلَىٰ طَعَامِ الْمِسْكِينِ (3) ድኻንም በማብላት ላይ የማያግባባው ሰው ነው፡፡ |
| فَوَيْلٌ لِّلْمُصَلِّينَ (4) ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡ |
| الَّذِينَ هُمْ عَن صَلَاتِهِمْ سَاهُونَ (5) ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡ |
| الَّذِينَ هُمْ يُرَاءُونَ (6) ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት፡፡ |
| وَيَمْنَعُونَ الْمَاعُونَ (7) የዕቃ ትውስትንም (ሰዎችን) የሚከለክሉ ለኾኑት (ወዮላቸው)፡፡ |