The Quran in Amharic - Surah Naziat translated into Amharic, Surah An-Naziat in Amharic. We provide accurate translation of Surah Naziat in Amharic - الأمهرية, Verses 46 - Surah Number 79 - Page 583.

| وَالنَّازِعَاتِ غَرْقًا (1) በኃይል አውጪዎች በኾኑት፤ |
| وَالنَّاشِطَاتِ نَشْطًا (2) በቀስታ መምዘዝንም መዘዦች በኾኑት፤ |
| وَالسَّابِحَاتِ سَبْحًا (3) መዋኘትም ዋኚዎች በኾኑት፤ |
| فَالسَّابِقَاتِ سَبْقًا (4) መቅደምንም ቀዳሚዎች በኾኑት፤ |
| فَالْمُدَبِّرَاتِ أَمْرًا (5) ነገርንም አስተናባሪዎች በኾኑት (መላእክት) እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡ |
| يَوْمَ تَرْجُفُ الرَّاجِفَةُ (6) ተርገፍጋፊይቱ (ምድር) በምትርገፈገፍበት ቀን፤ |
| تَتْبَعُهَا الرَّادِفَةُ (7) ለጣቂይቱ የምትከተላት ስትኾን (ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡ |
| قُلُوبٌ يَوْمَئِذٍ وَاجِفَةٌ (8) በዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው፡፡ |
| أَبْصَارُهَا خَاشِعَةٌ (9) ዓይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው፡፡ |
| يَقُولُونَ أَإِنَّا لَمَرْدُودُونَ فِي الْحَافِرَةِ (10) «እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ኹነታ ተመላሾች ነን?» ይላሉ፡፡ |
| أَإِذَا كُنَّا عِظَامًا نَّخِرَةً (11) «የበሰበሱ አጥንቶች በኾን ጊዜ (እንቀሰቀሳለን?)» |
| قَالُوا تِلْكَ إِذًا كَرَّةٌ خَاسِرَةٌ (12) «ይህቺ ያን ጊዜ ባለ ከሳራ መመለስ ናት» ይላሉ፡፡ |
| فَإِنَّمَا هِيَ زَجْرَةٌ وَاحِدَةٌ (13) እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ |
| فَإِذَا هُم بِالسَّاهِرَةِ (14) ወዲያውኑም እነርሱ እንቅልፍ በሌለባት (ምድር) ላይ ይኾናሉ፡፡ |
| هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ مُوسَىٰ (15) የሙሳ ወሬ መጣልህን |
| إِذْ نَادَاهُ رَبُّهُ بِالْوَادِ الْمُقَدَّسِ طُوًى (16) ጌታው በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ በጠራው ጊዜ፤ |
| اذْهَبْ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ إِنَّهُ طَغَىٰ (17) ወደ ፈርዖን ኺድ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡ |
| فَقُلْ هَل لَّكَ إِلَىٰ أَن تَزَكَّىٰ (18) በለውም፡- «ወደ መጥራራትህ ላንተ (መንገድ) አለህን?» |
| وَأَهْدِيَكَ إِلَىٰ رَبِّكَ فَتَخْشَىٰ (19) «ወደ ጌታህም ልመራህ ትፈራውም ዘንድ፤ (መንገድ አለህን?)» አለው፡፡ |
| فَأَرَاهُ الْآيَةَ الْكُبْرَىٰ (20) ታላቂቱንም ተዓምር አሳየው፡፡ |
| فَكَذَّبَ وَعَصَىٰ (21) አስተባበለም፤ አመጸም፡፡ |
| ثُمَّ أَدْبَرَ يَسْعَىٰ (22) ከዚያም (ለማጥፋት) የሚተጋ ኾኖ ዞረ፡፡ |
| فَحَشَرَ فَنَادَىٰ (23) (ሰራዊቶቹን) ሰበሰበም፤ ተጣራም፡፡ |
| فَقَالَ أَنَا رَبُّكُمُ الْأَعْلَىٰ (24) አለም፡- «እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ፡፡» |
| فَأَخَذَهُ اللَّهُ نَكَالَ الْآخِرَةِ وَالْأُولَىٰ (25) አላህም በኋለኛይቱና በፊተኛይቱ (ቃል) ቅጣት ያዘው፡፡ |
| إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَعِبْرَةً لِّمَن يَخْشَىٰ (26) በዚህ ውስጥ ለሚፈራ ሰው በእርግጥ መገምገሚያ አለበት፡፡ |
| أَأَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمِ السَّمَاءُ ۚ بَنَاهَا (27) ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? (አላህ) ገነባት፡፡ |
| رَفَعَ سَمْكَهَا فَسَوَّاهَا (28) ከፍታዋን አጓነ፤ አስተካከላትም፡፡ |
| وَأَغْطَشَ لَيْلَهَا وَأَخْرَجَ ضُحَاهَا (29) ሌሊቷንም አጨለመ፡፡ ቀንዋንም ገለጸ፡፡ |
| وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا (30) ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡ |
| أَخْرَجَ مِنْهَا مَاءَهَا وَمَرْعَاهَا (31) ውሃዋንና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ፡፡ |
| وَالْجِبَالَ أَرْسَاهَا (32) ጋራዎችንም አደላደላቸው፡፡ |
| مَتَاعًا لَّكُمْ وَلِأَنْعَامِكُمْ (33) ለእናንተና ለእንስሶቻችሁ መጣቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን አደረገ)፡፡ |
| فَإِذَا جَاءَتِ الطَّامَّةُ الْكُبْرَىٰ (34) ታላቂቱም መዐት በመጣች ጊዜ፣ |
| يَوْمَ يَتَذَكَّرُ الْإِنسَانُ مَا سَعَىٰ (35) ሰው ሁሉ የሠራውን በሚያስታውስበት ቀን፣ |
| وَبُرِّزَتِ الْجَحِيمُ لِمَن يَرَىٰ (36) ገሀነምም ለሚያይ ሰው በተገለጠች ጊዜ፣ |
| فَأَمَّا مَن طَغَىٰ (37) የካደ ሰውማ፣ |
| وَآثَرَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا (38) ቅርቢቱንም ሕይወት የመረጠ፣ |
| فَإِنَّ الْجَحِيمَ هِيَ الْمَأْوَىٰ (39) ገሀነም እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ |
| وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ (40) በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ |
| فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ (41) ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ |
| يَسْأَلُونَكَ عَنِ السَّاعَةِ أَيَّانَ مُرْسَاهَا (42) «ከሰዓቲቱ መቼ ነው መኾኛዋ?» ሲሉ ይጠይቁሃል፡፡ |
| فِيمَ أَنتَ مِن ذِكْرَاهَا (43) አንተ እርሷን ከማስታወስ በምን ውስጥ ነህ |
| إِلَىٰ رَبِّكَ مُنتَهَاهَا (44) (የዕውቀት) መጨረሻዋ ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ |
| إِنَّمَا أَنتَ مُنذِرُ مَن يَخْشَاهَا (45) አንተ የሚፈራትን ሰው አስፈራሪ ብቻ ነህ፡፡ |
| كَأَنَّهُمْ يَوْمَ يَرَوْنَهَا لَمْ يَلْبَثُوا إِلَّا عَشِيَّةً أَوْ ضُحَاهَا (46) እነርሱ በሚያዩዋት ቀን ያንዲት ቀን ምሽትን ወይም ረፏዷን እንጅ ያልቆዩ ይመስላሉ፡፡ |