The Quran in Amharic - Surah Takwir translated into Amharic, Surah At-Takwir in Amharic. We provide accurate translation of Surah Takwir in Amharic - الأمهرية, Verses 29 - Surah Number 81 - Page 586.
إِذَا الشَّمْسُ كُوِّرَتْ (1) ፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤ |
وَإِذَا النُّجُومُ انكَدَرَتْ (2) ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْجِبَالُ سُيِّرَتْ (3) ተራራዎችም በተነዱ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْعِشَارُ عُطِّلَتْ (4) የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْوُحُوشُ حُشِرَتْ (5) እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْبِحَارُ سُجِّرَتْ (6) ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤ |
وَإِذَا النُّفُوسُ زُوِّجَتْ (7) ነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْمَوْءُودَةُ سُئِلَتْ (8) በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤ |
بِأَيِّ ذَنبٍ قُتِلَتْ (9) በምን ወንጀል እንደ ተገደለች፤ |
وَإِذَا الصُّحُفُ نُشِرَتْ (10) ጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤ |
وَإِذَا السَّمَاءُ كُشِطَتْ (11) ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْجَحِيمُ سُعِّرَتْ (12) ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْجَنَّةُ أُزْلِفَتْ (13) ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤ |
عَلِمَتْ نَفْسٌ مَّا أَحْضَرَتْ (14) ነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤ |
فَلَا أُقْسِمُ بِالْخُنَّسِ (15) ተመላሾችም በኾኑት (ዐዋድያት) እምላለሁ፡፡ |
الْجَوَارِ الْكُنَّسِ (16) ኺያጆች ገቢዎች በኾኑት (ከዋክብት)፡፡ |
وَاللَّيْلِ إِذَا عَسْعَسَ (17) በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤ |
وَالصُّبْحِ إِذَا تَنَفَّسَ (18) በንጋቱም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)፡፡ |
إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ (19) እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡ |
ذِي قُوَّةٍ عِندَ ذِي الْعَرْشِ مَكِينٍ (20) የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡ |
مُّطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ (21) በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡ |
وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ (22) ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡ |
وَلَقَدْ رَآهُ بِالْأُفُقِ الْمُبِينِ (23) በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡ |
وَمَا هُوَ عَلَى الْغَيْبِ بِضَنِينٍ (24) እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡ |
وَمَا هُوَ بِقَوْلِ شَيْطَانٍ رَّجِيمٍ (25) እርሱም (ቁርኣን) የእርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም፡፡ |
فَأَيْنَ تَذْهَبُونَ (26) ታዲያ ወዴት ትኼዳላችሁ |
إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِّلْعَالَمِينَ (27) እርሱ የዓለማት መገሠጫ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ |
لِمَن شَاءَ مِنكُمْ أَن يَسْتَقِيمَ (28) ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)፡፡ |
وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ (29) የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡ |