The Quran in Amharic - Surah Al Ala translated into Amharic, Surah Al-Ala in Amharic. We provide accurate translation of Surah Al Ala in Amharic - الأمهرية, Verses 19 - Surah Number 87 - Page 591.

| سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى (1) ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡ |
| الَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ (2) የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡ |
| وَالَّذِي قَدَّرَ فَهَدَىٰ (3) የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡ |
| وَالَّذِي أَخْرَجَ الْمَرْعَىٰ (4) የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡ |
| فَجَعَلَهُ غُثَاءً أَحْوَىٰ (5) (ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡ |
| سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ (6) (ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡ |
| إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّهُ يَعْلَمُ الْجَهْرَ وَمَا يَخْفَىٰ (7) አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡ |
| وَنُيَسِّرُكَ لِلْيُسْرَىٰ (8) ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡ |
| فَذَكِّرْ إِن نَّفَعَتِ الذِّكْرَىٰ (9) ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡ |
| سَيَذَّكَّرُ مَن يَخْشَىٰ (10) (አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡ |
| وَيَتَجَنَّبُهَا الْأَشْقَى (11) መናጢውም ይርቃታል፡፡ |
| الَّذِي يَصْلَى النَّارَ الْكُبْرَىٰ (12) ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡ |
| ثُمَّ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحْيَىٰ (13) ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡ |
| قَدْ أَفْلَحَ مَن تَزَكَّىٰ (14) የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡ |
| وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّىٰ (15) የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡ |
| بَلْ تُؤْثِرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا (16) ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡ |
| وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ (17) መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡ |
| إِنَّ هَٰذَا لَفِي الصُّحُفِ الْأُولَىٰ (18) ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡ |
| صُحُفِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ (19) በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡ |