The Quran in Amharic - Surah Tariq translated into Amharic, Surah At-Tariq in Amharic. We provide accurate translation of Surah Tariq in Amharic - الأمهرية, Verses 17 - Surah Number 86 - Page 591.

| وَالسَّمَاءِ وَالطَّارِقِ (1) በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡ |
| وَمَا أَدْرَاكَ مَا الطَّارِقُ (2) የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ |
| النَّجْمُ الثَّاقِبُ (3) ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡ |
| إِن كُلُّ نَفْسٍ لَّمَّا عَلَيْهَا حَافِظٌ (4) ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ |
| فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ مِمَّ خُلِقَ (5) ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡ |
| خُلِقَ مِن مَّاءٍ دَافِقٍ (6) ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡ |
| يَخْرُجُ مِن بَيْنِ الصُّلْبِ وَالتَّرَائِبِ (7) ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡ |
| إِنَّهُ عَلَىٰ رَجْعِهِ لَقَادِرٌ (8) እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡ |
| يَوْمَ تُبْلَى السَّرَائِرُ (9) ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡ |
| فَمَا لَهُ مِن قُوَّةٍ وَلَا نَاصِرٍ (10) ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡ |
| وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الرَّجْعِ (11) የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡ |
| وَالْأَرْضِ ذَاتِ الصَّدْعِ (12) (በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤ |
| إِنَّهُ لَقَوْلٌ فَصْلٌ (13) እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡ |
| وَمَا هُوَ بِالْهَزْلِ (14) እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡ |
| إِنَّهُمْ يَكِيدُونَ كَيْدًا (15) እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡ |
| وَأَكِيدُ كَيْدًا (16) (እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡ |
| فَمَهِّلِ الْكَافِرِينَ أَمْهِلْهُمْ رُوَيْدًا (17) ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡ |