The Quran in Amharic - Surah Shams translated into Amharic, Surah Ash-Shams in Amharic. We provide accurate translation of Surah Shams in Amharic - الأمهرية, Verses 15 - Surah Number 91 - Page 595.

| وَالشَّمْسِ وَضُحَاهَا (1) በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡ |
| وَالْقَمَرِ إِذَا تَلَاهَا (2) በጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤ |
| وَالنَّهَارِ إِذَا جَلَّاهَا (3) በቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤ |
| وَاللَّيْلِ إِذَا يَغْشَاهَا (4) በሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤ |
| وَالسَّمَاءِ وَمَا بَنَاهَا (5) በሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤ |
| وَالْأَرْضِ وَمَا طَحَاهَا (6) በምድሪቱም በዘረጋትም፤ |
| وَنَفْسٍ وَمَا سَوَّاهَا (7) በነፍስም ባስተካከላትም፤ |
| فَأَلْهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقْوَاهَا (8) አመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡ |
| قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا (9) (ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡ |
| وَقَدْ خَابَ مَن دَسَّاهَا (10) (በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡ |
| كَذَّبَتْ ثَمُودُ بِطَغْوَاهَا (11) ሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡ |
| إِذِ انبَعَثَ أَشْقَاهَا (12) ጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡ |
| فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ اللَّهِ نَاقَةَ اللَّهِ وَسُقْيَاهَا (13) ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡ |
| فَكَذَّبُوهُ فَعَقَرُوهَا فَدَمْدَمَ عَلَيْهِمْ رَبُّهُم بِذَنبِهِمْ فَسَوَّاهَا (14) አስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡ |
| وَلَا يَخَافُ عُقْبَاهَا (15) ፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አያፈራም፡፡ |