The Quran in Amharic - Surah Al Balad translated into Amharic, Surah Al-Balad in Amharic. We provide accurate translation of Surah Al Balad in Amharic - الأمهرية, Verses 20 - Surah Number 90 - Page 594.

| لَا أُقْسِمُ بِهَٰذَا الْبَلَدِ (1) በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡ |
| وَأَنتَ حِلٌّ بِهَٰذَا الْبَلَدِ (2) አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡ |
| وَوَالِدٍ وَمَا وَلَدَ (3) በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡ |
| لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ فِي كَبَدٍ (4) ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡ |
| أَيَحْسَبُ أَن لَّن يَقْدِرَ عَلَيْهِ أَحَدٌ (5) በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን |
| يَقُولُ أَهْلَكْتُ مَالًا لُّبَدًا (6) «ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡ |
| أَيَحْسَبُ أَن لَّمْ يَرَهُ أَحَدٌ (7) አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን |
| أَلَمْ نَجْعَل لَّهُ عَيْنَيْنِ (8) ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን |
| وَلِسَانًا وَشَفَتَيْنِ (9) ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡ |
| وَهَدَيْنَاهُ النَّجْدَيْنِ (10) ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን |
| فَلَا اقْتَحَمَ الْعَقَبَةَ (11) ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡ |
| وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْعَقَبَةُ (12) ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ |
| فَكُّ رَقَبَةٍ (13) (እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡ |
| أَوْ إِطْعَامٌ فِي يَوْمٍ ذِي مَسْغَبَةٍ (14) ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡ |
| يَتِيمًا ذَا مَقْرَبَةٍ (15) የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤ |
| أَوْ مِسْكِينًا ذَا مَتْرَبَةٍ (16) ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡ |
| ثُمَّ كَانَ مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ وَتَوَاصَوْا بِالْمَرْحَمَةِ (17) (ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡ |
| أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ (18) እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡ |
| وَالَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا هُمْ أَصْحَابُ الْمَشْأَمَةِ (19) እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡ |
| عَلَيْهِمْ نَارٌ مُّؤْصَدَةٌ (20) በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡ |