The Quran in Amharic - Surah Duha translated into Amharic, Surah Ad-Dhuha in Amharic. We provide accurate translation of Surah Duha in Amharic - الأمهرية, Verses 11 - Surah Number 93 - Page 596.

| وَالضُّحَىٰ (1) በረፋዱ እምላለሁ፡፡ |
| وَاللَّيْلِ إِذَا سَجَىٰ (2) በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤ |
| مَا وَدَّعَكَ رَبُّكَ وَمَا قَلَىٰ (3) ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡ |
| وَلَلْآخِرَةُ خَيْرٌ لَّكَ مِنَ الْأُولَىٰ (4) መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡ |
| وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ (5) ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡ |
| أَلَمْ يَجِدْكَ يَتِيمًا فَآوَىٰ (6) የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)፡፡ |
| وَوَجَدَكَ ضَالًّا فَهَدَىٰ (7) የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡ |
| وَوَجَدَكَ عَائِلًا فَأَغْنَىٰ (8) ድኻም ኾነህ አገኘህ፤ አከበረህም፡፡ |
| فَأَمَّا الْيَتِيمَ فَلَا تَقْهَرْ (9) የቲምንማ አትጨቁን፡፡ |
| وَأَمَّا السَّائِلَ فَلَا تَنْهَرْ (10) ለማኝንም አትገላምጥ፡፡ |
| وَأَمَّا بِنِعْمَةِ رَبِّكَ فَحَدِّثْ (11) በጌታህም ጸጋ አውራ፤ (ግለጻት)፡፡ |