The Quran in Amharic - Surah Humazah translated into Amharic, Surah Al-Humazah in Amharic. We provide accurate translation of Surah Humazah in Amharic - الأمهرية, Verses 9 - Surah Number 104 - Page 601.

| وَيْلٌ لِّكُلِّ هُمَزَةٍ لُّمَزَةٍ (1) ለሃሜተኛ ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት፡፡ |
| الَّذِي جَمَعَ مَالًا وَعَدَّدَهُ (2) ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበውም) ለኾነ ፤(ወዮለት)፡፡ |
| يَحْسَبُ أَنَّ مَالَهُ أَخْلَدَهُ (3) ገንዘቡ የሚያዘወትረው መኾኑን ያስባል፡፡ |
| كَلَّا ۖ لَيُنبَذَنَّ فِي الْحُطَمَةِ (4) ይከልከል፤ በሰባሪይቱ (እሳት) ውስጥ በእርግጥ ይጣላል፡፡ |
| وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْحُطَمَةُ (5) ሰባሪይቱም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ |
| نَارُ اللَّهِ الْمُوقَدَةُ (6) የተነደደችው የአላህ እሳት ናት፡፡ |
| الَّتِي تَطَّلِعُ عَلَى الْأَفْئِدَةِ (7) ያቺ በልቦች ላይ የምትዘልቅ የኾነችው፡፡ |
| إِنَّهَا عَلَيْهِم مُّؤْصَدَةٌ (8) እርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋጀች ናት፡፡ |
| فِي عَمَدٍ مُّمَدَّدَةٍ (9) በተዘረጋች አዕማድ ውስጥ (የተዘጋች ናት)፡፡ |