القرآن باللغة الأمهرية - سورة الطارق مترجمة إلى اللغة الأمهرية، Surah Tariq in Amharic. نوفر ترجمة دقيقة سورة الطارق باللغة الأمهرية - Amharic, الآيات 17 - رقم السورة 86 - الصفحة 591.
وَالسَّمَاءِ وَالطَّارِقِ (1) በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡ |
وَمَا أَدْرَاكَ مَا الطَّارِقُ (2) የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ |
النَّجْمُ الثَّاقِبُ (3) ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡ |
إِن كُلُّ نَفْسٍ لَّمَّا عَلَيْهَا حَافِظٌ (4) ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ |
فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ مِمَّ خُلِقَ (5) ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡ |
خُلِقَ مِن مَّاءٍ دَافِقٍ (6) ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡ |
يَخْرُجُ مِن بَيْنِ الصُّلْبِ وَالتَّرَائِبِ (7) ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡ |
إِنَّهُ عَلَىٰ رَجْعِهِ لَقَادِرٌ (8) እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡ |
يَوْمَ تُبْلَى السَّرَائِرُ (9) ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡ |
فَمَا لَهُ مِن قُوَّةٍ وَلَا نَاصِرٍ (10) ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡ |
وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الرَّجْعِ (11) የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡ |
وَالْأَرْضِ ذَاتِ الصَّدْعِ (12) (በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤ |
إِنَّهُ لَقَوْلٌ فَصْلٌ (13) እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡ |
وَمَا هُوَ بِالْهَزْلِ (14) እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡ |
إِنَّهُمْ يَكِيدُونَ كَيْدًا (15) እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡ |
وَأَكِيدُ كَيْدًا (16) (እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡ |
فَمَهِّلِ الْكَافِرِينَ أَمْهِلْهُمْ رُوَيْدًا (17) ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡ |