القرآن باللغة الأمهرية - سورة البلد مترجمة إلى اللغة الأمهرية، Surah Al Balad in Amharic. نوفر ترجمة دقيقة سورة البلد باللغة الأمهرية - Amharic, الآيات 20 - رقم السورة 90 - الصفحة 594.
لَا أُقْسِمُ بِهَٰذَا الْبَلَدِ (1) በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡ |
وَأَنتَ حِلٌّ بِهَٰذَا الْبَلَدِ (2) አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡ |
وَوَالِدٍ وَمَا وَلَدَ (3) በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡ |
لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ فِي كَبَدٍ (4) ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡ |
أَيَحْسَبُ أَن لَّن يَقْدِرَ عَلَيْهِ أَحَدٌ (5) በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን |
يَقُولُ أَهْلَكْتُ مَالًا لُّبَدًا (6) «ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡ |
أَيَحْسَبُ أَن لَّمْ يَرَهُ أَحَدٌ (7) አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን |
أَلَمْ نَجْعَل لَّهُ عَيْنَيْنِ (8) ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን |
وَلِسَانًا وَشَفَتَيْنِ (9) ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡ |
وَهَدَيْنَاهُ النَّجْدَيْنِ (10) ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን |
فَلَا اقْتَحَمَ الْعَقَبَةَ (11) ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡ |
وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْعَقَبَةُ (12) ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ |
فَكُّ رَقَبَةٍ (13) (እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡ |
أَوْ إِطْعَامٌ فِي يَوْمٍ ذِي مَسْغَبَةٍ (14) ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡ |
يَتِيمًا ذَا مَقْرَبَةٍ (15) የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤ |
أَوْ مِسْكِينًا ذَا مَتْرَبَةٍ (16) ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡ |
ثُمَّ كَانَ مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ وَتَوَاصَوْا بِالْمَرْحَمَةِ (17) (ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡ |
أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ (18) እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡ |
وَالَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا هُمْ أَصْحَابُ الْمَشْأَمَةِ (19) እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡ |
عَلَيْهِمْ نَارٌ مُّؤْصَدَةٌ (20) በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡ |