القرآن باللغة الأمهرية - سورة المعارج مترجمة إلى اللغة الأمهرية، Surah Maarij in Amharic. نوفر ترجمة دقيقة سورة المعارج باللغة الأمهرية - Amharic, الآيات 44 - رقم السورة 70 - الصفحة 568.

| سَأَلَ سَائِلٌ بِعَذَابٍ وَاقِعٍ (1) ወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡ |
| لِّلْكَافِرِينَ لَيْسَ لَهُ دَافِعٌ (2) በከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡ |
| مِّنَ اللَّهِ ذِي الْمَعَارِجِ (3) የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡ |
| تَعْرُجُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ (4) መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡ |
| فَاصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًا (5) መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡ |
| إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيدًا (6) እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡ |
| وَنَرَاهُ قَرِيبًا (7) እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡ |
| يَوْمَ تَكُونُ السَّمَاءُ كَالْمُهْلِ (8) ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡ |
| وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِ (9) ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡ |
| وَلَا يَسْأَلُ حَمِيمٌ حَمِيمًا (10) ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡ |
| يُبَصَّرُونَهُمْ ۚ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ (11) (ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡ |
| وَصَاحِبَتِهِ وَأَخِيهِ (12) በሚስቱም በወንድሙም፡፡ |
| وَفَصِيلَتِهِ الَّتِي تُؤْوِيهِ (13) በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡ |
| وَمَن فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ يُنجِيهِ (14) በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡ |
| كَلَّا ۖ إِنَّهَا لَظَىٰ (15) ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡ |
| نَزَّاعَةً لِّلشَّوَىٰ (16) የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡ |
| تَدْعُو مَنْ أَدْبَرَ وَتَوَلَّىٰ (17) (ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡ |
| وَجَمَعَ فَأَوْعَىٰ (18) ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡ |
| ۞ إِنَّ الْإِنسَانَ خُلِقَ هَلُوعًا (19) ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡ |
| إِذَا مَسَّهُ الشَّرُّ جَزُوعًا (20) ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡ |
| وَإِذَا مَسَّهُ الْخَيْرُ مَنُوعًا (21) መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡ |
| إِلَّا الْمُصَلِّينَ (22) ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡ |
| الَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ دَائِمُونَ (23) እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡ |
| وَالَّذِينَ فِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ مَّعْلُومٌ (24) እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡ |
| لِّلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ (25) ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡ |
| وَالَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوْمِ الدِّينِ (26) እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡ |
| وَالَّذِينَ هُم مِّنْ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشْفِقُونَ (27) እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡ |
| إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمْ غَيْرُ مَأْمُونٍ (28) የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡ |
| وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ (29) እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ |
| إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ (30) በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ |
| فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَ (31) ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡ |
| وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ (32) እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ |
| وَالَّذِينَ هُم بِشَهَادَاتِهِمْ قَائِمُونَ (33) እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡ |
| وَالَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ يُحَافِظُونَ (34) እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡ |
| أُولَٰئِكَ فِي جَنَّاتٍ مُّكْرَمُونَ (35) እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡ |
| فَمَالِ الَّذِينَ كَفَرُوا قِبَلَكَ مُهْطِعِينَ (36) ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው |
| عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ عِزِينَ (37) ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡ |
| أَيَطْمَعُ كُلُّ امْرِئٍ مِّنْهُمْ أَن يُدْخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٍ (38) ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን |
| كَلَّا ۖ إِنَّا خَلَقْنَاهُم مِّمَّا يَعْلَمُونَ (39) ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡ |
| فَلَا أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَ (40) በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ |
| عَلَىٰ أَن نُّبَدِّلَ خَيْرًا مِّنْهُمْ وَمَا نَحْنُ بِمَسْبُوقِينَ (41) ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡ |
| فَذَرْهُمْ يَخُوضُوا وَيَلْعَبُوا حَتَّىٰ يُلَاقُوا يَوْمَهُمُ الَّذِي يُوعَدُونَ (42) ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡ |
| يَوْمَ يَخْرُجُونَ مِنَ الْأَجْدَاثِ سِرَاعًا كَأَنَّهُمْ إِلَىٰ نُصُبٍ يُوفِضُونَ (43) ወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡ |
| خَاشِعَةً أَبْصَارُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ ۚ ذَٰلِكَ الْيَوْمُ الَّذِي كَانُوا يُوعَدُونَ (44) ዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡ |