القرآن باللغة الأمهرية - سورة العلق مترجمة إلى اللغة الأمهرية، Surah Al Alaq in Amharic. نوفر ترجمة دقيقة سورة العلق باللغة الأمهرية - Amharic, الآيات 19 - رقم السورة 96 - الصفحة 597.
اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ (1) አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡ |
خَلَقَ الْإِنسَانَ مِنْ عَلَقٍ (2) ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ |
اقْرَأْ وَرَبُّكَ الْأَكْرَمُ (3) አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ |
الَّذِي عَلَّمَ بِالْقَلَمِ (4) ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡ |
عَلَّمَ الْإِنسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ (5) ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡ |
كَلَّا إِنَّ الْإِنسَانَ لَيَطْغَىٰ (6) በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡ |
أَن رَّآهُ اسْتَغْنَىٰ (7) ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡ |
إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ الرُّجْعَىٰ (8) መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ |
أَرَأَيْتَ الَّذِي يَنْهَىٰ (9) አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡ |
عَبْدًا إِذَا صَلَّىٰ (10) ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤ |
أَرَأَيْتَ إِن كَانَ عَلَى الْهُدَىٰ (11) አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤ |
أَوْ أَمَرَ بِالتَّقْوَىٰ (12) ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤ |
أَرَأَيْتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ (13) አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤ |
أَلَمْ يَعْلَم بِأَنَّ اللَّهَ يَرَىٰ (14) አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን |
كَلَّا لَئِن لَّمْ يَنتَهِ لَنَسْفَعًا بِالنَّاصِيَةِ (15) ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡ |
نَاصِيَةٍ كَاذِبَةٍ خَاطِئَةٍ (16) ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡ |
فَلْيَدْعُ نَادِيَهُ (17) ሸንጎውንም ይጥራ፡፡ |
سَنَدْعُ الزَّبَانِيَةَ (18) (እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡ |
كَلَّا لَا تُطِعْهُ وَاسْجُدْ وَاقْتَرِب ۩ (19) ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡ |