القرآن باللغة الأمهرية - سورة عبس مترجمة إلى اللغة الأمهرية، Surah Abasa in Amharic. نوفر ترجمة دقيقة سورة عبس باللغة الأمهرية - Amharic, الآيات 42 - رقم السورة 80 - الصفحة 585.

| عَبَسَ وَتَوَلَّىٰ (1) ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡ |
| أَن جَاءَهُ الْأَعْمَىٰ (2) ዕውሩ ስለ መጣው፡፡ |
| وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّهُ يَزَّكَّىٰ (3) ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡፡ |
| أَوْ يَذَّكَّرُ فَتَنفَعَهُ الذِّكْرَىٰ (4) ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡፡ |
| أَمَّا مَنِ اسْتَغْنَىٰ (5) የተብቃቃው ሰውማ፤ |
| فَأَنتَ لَهُ تَصَدَّىٰ (6) አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡ |
| وَمَا عَلَيْكَ أَلَّا يَزَّكَّىٰ (7) ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡፡ |
| وَأَمَّا مَن جَاءَكَ يَسْعَىٰ (8) እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤ |
| وَهُوَ يَخْشَىٰ (9) እርሱ (አላህን) የሚፈራ ሲኾን፤ |
| فَأَنتَ عَنْهُ تَلَهَّىٰ (10) አንተ ከእርሱ ትዝዘናጋለህ፡፡ |
| كَلَّا إِنَّهَا تَذْكِرَةٌ (11) ተከልከል፡፡ እርሷ ማስገንዘቢያ ናት፡፡ |
| فَمَن شَاءَ ذَكَرَهُ (12) የሻም ሰው (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል፡፡ |
| فِي صُحُفٍ مُّكَرَّمَةٍ (13) በተከበሩ ጽሑፎች ውስጥ ነው፡፡ |
| مَّرْفُوعَةٍ مُّطَهَّرَةٍ (14) ከፍ በተደረገች ንጹሕ በተደረገች (ጽሑፍ ውስጥ ነው)፡፡ |
| بِأَيْدِي سَفَرَةٍ (15) በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡ |
| كِرَامٍ بَرَرَةٍ (16) የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡ |
| قُتِلَ الْإِنسَانُ مَا أَكْفَرَهُ (17) ሰው ተረገመ፤ ምን ከሓዲ አደረገው |
| مِنْ أَيِّ شَيْءٍ خَلَقَهُ (18) (ጌታው) በምን ነገር ፈጠረው? (አያስብምን) |
| مِن نُّطْفَةٍ خَلَقَهُ فَقَدَّرَهُ (19) ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነውም፡፡ |
| ثُمَّ السَّبِيلَ يَسَّرَهُ (20) ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው፡፡ |
| ثُمَّ أَمَاتَهُ فَأَقْبَرَهُ (21) ከዚያም ገደለው፤ እንዲቀበርም አደረገው፡፡ |
| ثُمَّ إِذَا شَاءَ أَنشَرَهُ (22) ከዚያም (ማንሳቱን) በሻ ጊዜ ያስነሳዋል፡፡ |
| كَلَّا لَمَّا يَقْضِ مَا أَمَرَهُ (23) በእውነት ያንን (ጌታው) ያዘዘውን ገና አልፈጸመም፡፡ |
| فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ إِلَىٰ طَعَامِهِ (24) ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፡፡ |
| أَنَّا صَبَبْنَا الْمَاءَ صَبًّا (25) እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መኾናችንን፡፡ |
| ثُمَّ شَقَقْنَا الْأَرْضَ شَقًّا (26) ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤ |
| فَأَنبَتْنَا فِيهَا حَبًّا (27) በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤ |
| وَعِنَبًا وَقَضْبًا (28) ወይንንም፤ እርጥብ ያበቀልን፤ |
| وَزَيْتُونًا وَنَخْلًا (29) የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤ |
| وَحَدَائِقَ غُلْبًا (30) ጭፍቆች አትክልቶችንም፤ |
| وَفَاكِهَةً وَأَبًّا (31) ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መኾናችንን ይመልከት)፡፡ |
| مَّتَاعًا لَّكُمْ وَلِأَنْعَامِكُمْ (32) ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን ሠራን)፡፡ |
| فَإِذَا جَاءَتِ الصَّاخَّةُ (33) አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤ |
| يَوْمَ يَفِرُّ الْمَرْءُ مِنْ أَخِيهِ (34) ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤ |
| وَأُمِّهِ وَأَبِيهِ (35) ከናቱም ካባቱም፤ |
| وَصَاحِبَتِهِ وَبَنِيهِ (36) ከሚስቱም ከልጁም፤ |
| لِكُلِّ امْرِئٍ مِّنْهُمْ يَوْمَئِذٍ شَأْنٌ يُغْنِيهِ (37) ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ኹነታ አልለው፡፡ |
| وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ مُّسْفِرَةٌ (38) ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፤ |
| ضَاحِكَةٌ مُّسْتَبْشِرَةٌ (39) ሳቂዎችም ተደሳቾችም ናቸው፡፡ |
| وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ عَلَيْهَا غَبَرَةٌ (40) ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አልለባቸው፤ |
| تَرْهَقُهَا قَتَرَةٌ (41) ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤ |
| أُولَٰئِكَ هُمُ الْكَفَرَةُ الْفَجَرَةُ (42) እነዚያ እነሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡ |