القرآن باللغة الأمهرية - سورة الزلزلة مترجمة إلى اللغة الأمهرية، Surah Zalzalah in Amharic. نوفر ترجمة دقيقة سورة الزلزلة باللغة الأمهرية - Amharic, الآيات 8 - رقم السورة 99 - الصفحة 599.
إِذَا زُلْزِلَتِ الْأَرْضُ زِلْزَالَهَا (1) ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤ |
وَأَخْرَجَتِ الْأَرْضُ أَثْقَالَهَا (2) ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤ |
وَقَالَ الْإِنسَانُ مَا لَهَا (3) ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤ |
يَوْمَئِذٍ تُحَدِّثُ أَخْبَارَهَا (4) በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡ |
بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَىٰ لَهَا (5) ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡ |
يَوْمَئِذٍ يَصْدُرُ النَّاسُ أَشْتَاتًا لِّيُرَوْا أَعْمَالَهُمْ (6) በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡ |
فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ (7) የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡ |
وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ (8) የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡ |