القرآن باللغة الأمهرية - سورة الإنفطار مترجمة إلى اللغة الأمهرية، Surah Infitar in Amharic. نوفر ترجمة دقيقة سورة الإنفطار باللغة الأمهرية - Amharic, الآيات 19 - رقم السورة 82 - الصفحة 587.
إِذَا السَّمَاءُ انفَطَرَتْ (1) ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْكَوَاكِبُ انتَثَرَتْ (2) ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْبِحَارُ فُجِّرَتْ (3) ባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْقُبُورُ بُعْثِرَتْ (4) መቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤ |
عَلِمَتْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ وَأَخَّرَتْ (5) ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡ |
يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ الْكَرِيمِ (6) አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ |
الَّذِي خَلَقَكَ فَسَوَّاكَ فَعَدَلَكَ (7) በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡ |
فِي أَيِّ صُورَةٍ مَّا شَاءَ رَكَّبَكَ (8) በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡ |
كَلَّا بَلْ تُكَذِّبُونَ بِالدِّينِ (9) ተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡ |
وَإِنَّ عَلَيْكُمْ لَحَافِظِينَ (10) በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤ |
كِرَامًا كَاتِبِينَ (11) የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡ |
يَعْلَمُونَ مَا تَفْعَلُونَ (12) የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ፡፡ |
إِنَّ الْأَبْرَارَ لَفِي نَعِيمٍ (13) እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በገነት ውስጥ ናቸው፡፡ |
وَإِنَّ الْفُجَّارَ لَفِي جَحِيمٍ (14) ከሓዲዎቹም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው፡፡ |
يَصْلَوْنَهَا يَوْمَ الدِّينِ (15) በፍርዱ ቀን ይገቧታል፡፡ |
وَمَا هُمْ عَنْهَا بِغَائِبِينَ (16) እነርሱም ከርሷ ራቂዎች አይደሉም፡፡ |
وَمَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الدِّينِ (17) የፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ |
ثُمَّ مَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الدِّينِ (18) ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ |
يَوْمَ لَا تَمْلِكُ نَفْسٌ لِّنَفْسٍ شَيْئًا ۖ وَالْأَمْرُ يَوْمَئِذٍ لِّلَّهِ (19) (እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፡፡ |