القرآن باللغة الأمهرية - سورة الانشقاق مترجمة إلى اللغة الأمهرية، Surah Inshiqaq in Amharic. نوفر ترجمة دقيقة سورة الانشقاق باللغة الأمهرية - Amharic, الآيات 25 - رقم السورة 84 - الصفحة 589.

| إِذَا السَّمَاءُ انشَقَّتْ (1) ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤ |
| وَأَذِنَتْ لِرَبِّهَا وَحُقَّتْ (2) ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤ |
| وَإِذَا الْأَرْضُ مُدَّتْ (3) ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤ |
| وَأَلْقَتْ مَا فِيهَا وَتَخَلَّتْ (4) በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤ |
| وَأَذِنَتْ لِرَبِّهَا وَحُقَّتْ (5) ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡ |
| يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَىٰ رَبِّكَ كَدْحًا فَمُلَاقِيهِ (6) አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡ |
| فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ (7) መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤ |
| فَسَوْفَ يُحَاسَبُ حِسَابًا يَسِيرًا (8) በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡ |
| وَيَنقَلِبُ إِلَىٰ أَهْلِهِ مَسْرُورًا (9) ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡ |
| وَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ وَرَاءَ ظَهْرِهِ (10) መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤ |
| فَسَوْفَ يَدْعُو ثُبُورًا (11) (ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡ |
| وَيَصْلَىٰ سَعِيرًا (12) የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡ |
| إِنَّهُ كَانَ فِي أَهْلِهِ مَسْرُورًا (13) እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡ |
| إِنَّهُ ظَنَّ أَن لَّن يَحُورَ (14) እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡ |
| بَلَىٰ إِنَّ رَبَّهُ كَانَ بِهِ بَصِيرًا (15) አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡ |
| فَلَا أُقْسِمُ بِالشَّفَقِ (16) አትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡ |
| وَاللَّيْلِ وَمَا وَسَقَ (17) በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤ |
| وَالْقَمَرِ إِذَا اتَّسَقَ (18) በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡ |
| لَتَرْكَبُنَّ طَبَقًا عَن طَبَقٍ (19) ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡ |
| فَمَا لَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ (20) የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው |
| وَإِذَا قُرِئَ عَلَيْهِمُ الْقُرْآنُ لَا يَسْجُدُونَ ۩ (21) በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው) |
| بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا يُكَذِّبُونَ (22) በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡ |
| وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُوعُونَ (23) አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡ |
| فَبَشِّرْهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ (24) በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡ |
| إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ أَجْرٌ غَيْرُ مَمْنُونٍ (25) ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡ |