القرآن باللغة الأمهرية - سورة المطففين مترجمة إلى اللغة الأمهرية، Surah Mutaffifin in Amharic. نوفر ترجمة دقيقة سورة المطففين باللغة الأمهرية - Amharic, الآيات 36 - رقم السورة 83 - الصفحة 587.
وَيْلٌ لِّلْمُطَفِّفِينَ (1) ለሰላቢዎች ወዮላቸው፡፡ |
الَّذِينَ إِذَا اكْتَالُوا عَلَى النَّاسِ يَسْتَوْفُونَ (2) ለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፡፡ |
وَإِذَا كَالُوهُمْ أَو وَّزَنُوهُمْ يُخْسِرُونَ (3) ለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡ |
أَلَا يَظُنُّ أُولَٰئِكَ أَنَّهُم مَّبْعُوثُونَ (4) እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መኾናቸውን አያውቁምን |
لِيَوْمٍ عَظِيمٍ (5) በታላቁ ቀን፡፡ |
يَوْمَ يَقُومُ النَّاسُ لِرَبِّ الْعَالَمِينَ (6) ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ)፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መኾናቸውን)፡፡ |
كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ (7) በእውነት የከሓዲዎቹ (የሰላቢዎቹ) መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፡፡ |
وَمَا أَدْرَاكَ مَا سِجِّينٌ (8) ሲጂንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ |
كِتَابٌ مَّرْقُومٌ (9) የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡ |
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ (10) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
الَّذِينَ يُكَذِّبُونَ بِيَوْمِ الدِّينِ (11) ለእነዚያ በፍርዱ ቀን ለሚያስተባብሉት፡፡ |
وَمَا يُكَذِّبُ بِهِ إِلَّا كُلُّ مُعْتَدٍ أَثِيمٍ (12) በእርሱም ወሰን አላፊ ኀጢአተኛ ሁሉ እንጅ ሌላ አያስተባብልም፡፡ |
إِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِ آيَاتُنَا قَالَ أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَ (13) አንቀጾቻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡ |
كَلَّا ۖ بَلْ ۜ رَانَ عَلَىٰ قُلُوبِهِم مَّا كَانُوا يَكْسِبُونَ (14) ይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡ |
كَلَّا إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ (15) ይከልከሉ፤ እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው (ማየት) ተጋራጆች ናቸው፡፡ |
ثُمَّ إِنَّهُمْ لَصَالُو الْجَحِيمِ (16) ከዚያም እነርሱ በእርግጥ ገሀነምን ገቢዎች ናቸው፡፡ |
ثُمَّ يُقَالُ هَٰذَا الَّذِي كُنتُم بِهِ تُكَذِّبُونَ (17) ከዚያም «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው» ይባላሉ፡፡ |
كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ (18) በእውነቱ የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው፡፡ |
وَمَا أَدْرَاكَ مَا عِلِّيُّونَ (19) ዒሊዮንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ |
كِتَابٌ مَّرْقُومٌ (20) የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡ |
يَشْهَدُهُ الْمُقَرَّبُونَ (21) ባለሟልዎቹ ይጣዱታል፡፡ |
إِنَّ الْأَبْرَارَ لَفِي نَعِيمٍ (22) እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡ |
عَلَى الْأَرَائِكِ يَنظُرُونَ (23) በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው ይመለከታሉ፡፡ |
تَعْرِفُ فِي وُجُوهِهِمْ نَضْرَةَ النَّعِيمِ (24) በፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ታውቃለህ፡፡ |
يُسْقَوْنَ مِن رَّحِيقٍ مَّخْتُومٍ (25) ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ |
خِتَامُهُ مِسْكٌ ۚ وَفِي ذَٰلِكَ فَلْيَتَنَافَسِ الْمُتَنَافِسُونَ (26) ማተሚያው ምስክ ከኾነ፤ በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ፡፡ |
وَمِزَاجُهُ مِن تَسْنِيمٍ (27) መበረዣውም ከተስኒም ነው፡፡ |
عَيْنًا يَشْرَبُ بِهَا الْمُقَرَّبُونَ (28) ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡ |
إِنَّ الَّذِينَ أَجْرَمُوا كَانُوا مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا يَضْحَكُونَ (29) እነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ፡፡ |
وَإِذَا مَرُّوا بِهِمْ يَتَغَامَزُونَ (30) በእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር፡፡ |
وَإِذَا انقَلَبُوا إِلَىٰ أَهْلِهِمُ انقَلَبُوا فَكِهِينَ (31) ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር፡፡ |
وَإِذَا رَأَوْهُمْ قَالُوا إِنَّ هَٰؤُلَاءِ لَضَالُّونَ (32) ባዩዋቸውም ጊዜ «እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው» ይሉ ነበር፡፡ |
وَمَا أُرْسِلُوا عَلَيْهِمْ حَافِظِينَ (33) በነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ፡፡ |
فَالْيَوْمَ الَّذِينَ آمَنُوا مِنَ الْكُفَّارِ يَضْحَكُونَ (34) ዛሬ (በትንሣኤ ቀን) እነዚያ ያመኑት በከሓዲዎቹ ይስቃሉ፡፡ |
عَلَى الْأَرَائِكِ يَنظُرُونَ (35) በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው የሚመለከቱ ሲኾኑ (ይስቃሉ)፡፡ |
هَلْ ثُوِّبَ الْكُفَّارُ مَا كَانُوا يَفْعَلُونَ (36) ከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)፡፡ |