القرآن باللغة الأمهرية - سورة البروج مترجمة إلى اللغة الأمهرية، Surah Buruj in Amharic. نوفر ترجمة دقيقة سورة البروج باللغة الأمهرية - Amharic, الآيات 22 - رقم السورة 85 - الصفحة 590.

| وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الْبُرُوجِ (1) የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡ |
| وَالْيَوْمِ الْمَوْعُودِ (2) በተቀጠረው ቀንም፤ |
| وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ (3) በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡ |
| قُتِلَ أَصْحَابُ الْأُخْدُودِ (4) የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡ |
| النَّارِ ذَاتِ الْوَقُودِ (5) የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡ |
| إِذْ هُمْ عَلَيْهَا قُعُودٌ (6) እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡ |
| وَهُمْ عَلَىٰ مَا يَفْعَلُونَ بِالْمُؤْمِنِينَ شُهُودٌ (7) እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡ |
| وَمَا نَقَمُوا مِنْهُمْ إِلَّا أَن يُؤْمِنُوا بِاللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَمِيدِ (8) ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡ |
| الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ (9) በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡ |
| إِنَّ الَّذِينَ فَتَنُوا الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ الْحَرِيقِ (10) እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡ |
| إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْكَبِيرُ (11) እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡ |
| إِنَّ بَطْشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ (12) የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡ |
| إِنَّهُ هُوَ يُبْدِئُ وَيُعِيدُ (13) እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡ |
| وَهُوَ الْغَفُورُ الْوَدُودُ (14) እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡ |
| ذُو الْعَرْشِ الْمَجِيدُ (15) የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡ |
| فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ (16) የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡ |
| هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ الْجُنُودِ (17) የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን |
| فِرْعَوْنَ وَثَمُودَ (18) የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡ |
| بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي تَكْذِيبٍ (19) በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡ |
| وَاللَّهُ مِن وَرَائِهِم مُّحِيطٌ (20) አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡ |
| بَلْ هُوَ قُرْآنٌ مَّجِيدٌ (21) ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡ |
| فِي لَوْحٍ مَّحْفُوظٍ (22) የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡ |