القرآن باللغة الأمهرية - سورة الليل مترجمة إلى اللغة الأمهرية، Surah Lail in Amharic. نوفر ترجمة دقيقة سورة الليل باللغة الأمهرية - Amharic, الآيات 21 - رقم السورة 92 - الصفحة 595.

| وَاللَّيْلِ إِذَا يَغْشَىٰ (1) በሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡ |
| وَالنَّهَارِ إِذَا تَجَلَّىٰ (2) በቀኑም፤ በተገለጸ ጊዜ፡፡ |
| وَمَا خَلَقَ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ (3) ወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡ |
| إِنَّ سَعْيَكُمْ لَشَتَّىٰ (4) ሥራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው፡፡ |
| فَأَمَّا مَنْ أَعْطَىٰ وَاتَّقَىٰ (5) የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፡፡ |
| وَصَدَّقَ بِالْحُسْنَىٰ (6) በመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤ |
| فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْيُسْرَىٰ (7) ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ |
| وَأَمَّا مَن بَخِلَ وَاسْتَغْنَىٰ (8) የሰሰተ ሰውማ የተብቃቃም፤ (በራሱ የተመካ)፤ |
| وَكَذَّبَ بِالْحُسْنَىٰ (9) በመልካሚቱ (እምነት) ያሰተባበለም፤ |
| فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْعُسْرَىٰ (10) ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ |
| وَمَا يُغْنِي عَنْهُ مَالُهُ إِذَا تَرَدَّىٰ (11) በወደቀም ጊዜ ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡ |
| إِنَّ عَلَيْنَا لَلْهُدَىٰ (12) ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን፡፡ |
| وَإِنَّ لَنَا لَلْآخِرَةَ وَالْأُولَىٰ (13) መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛ ናቸው፡፡ |
| فَأَنذَرْتُكُمْ نَارًا تَلَظَّىٰ (14) የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ (በላቸው)፡፡ |
| لَا يَصْلَاهَا إِلَّا الْأَشْقَى (15) ከጠማማ በቀር ሌላ የማይገባት የኾነችን፡፡ |
| الَّذِي كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ (16) ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝ የሸሸው፡፡ |
| وَسَيُجَنَّبُهَا الْأَتْقَى (17) አላህን በጣም ፈሪውም በእርግጥ ይርቃታል፡፡ |
| الَّذِي يُؤْتِي مَالَهُ يَتَزَكَّىٰ (18) ያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው፡፡ |
| وَمَا لِأَحَدٍ عِندَهُ مِن نِّعْمَةٍ تُجْزَىٰ (19) ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡ |
| إِلَّا ابْتِغَاءَ وَجْهِ رَبِّهِ الْأَعْلَىٰ (20) ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡ |
| وَلَسَوْفَ يَرْضَىٰ (21) ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡ |